” ከ47 በመቶ በላይ አሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከፍጥነት ወሰን በላይ ነው የሚያሽከረክሩት ! ”
የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኀበር ዘርፉን በተመለከተ አዘጋጅቶት በነበረው መድረክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጀመንት ባለስልጣን መጥተው የነበሩት አቶ ደረጀ የተባሉ አካል ” በየዓመቱ ከ2000 እስከ 300ዐ ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ስልጠና እንደሚሰጡ፣ ኢንፍራስትራክቸር በተለይ ለአካል ጉዳተኞች በልዩ ሁኔታ ተይዞ መሰራት እንዳለበት፣ አቅም በፈቀደ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
” ነገር ግን የትራፊክ ግጭቱ ስታቲስቲክሱ ሲታይ በዓመት አዲስ አበባ ከተማ ብቻ 401 ሰው ይሞታል። በአመት 401 ሰው ይሞታል ማለት በቀን ከ1 ሰው በላይ ይሞታል ማለት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
” ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የሚፈጠረው ግጭት ደግሞ መቆጣጠር የሚቻል፤ በሰዎች ስህተት የሚፈጠር እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት “ብለዋል።
” አንድ ክርክር አለ የትራፊክ አደጋ ነው ወይስ ግጭት ነው? የሚል። ከ95 በመቶ በላይ በሰዎች ባህሪ ላይ ሰርተን ለውጥ ማምጣት፤ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎችን ማክበር የምንችል ከሆነ ግጭቶችን መቀነስ የምንችልበት እድል ሰፊ ስለሆነ አደጋ ተብሎ ሊያዙ የሚገባ አይደሉም የሚል መከራከሪያ ይነሳል ” ነው ያሉት።
” እውነት ነው፤ አንደኛው በአዲስ አበባ ላይ የግጭት አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ፍጥነት ነው። ከ47 በመቶ በላይ አሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከፍጥነት ወሰን በላይ ነው የሚያሽከረክሩት ” ብለው፣ ” ስለዚህ አንድ አካል ጉዳተኛ ዜብራ መንገድ እያቋረጠ እያለ በፍጥነት የሚመጣ አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን ተቆጣጥሮ ከአደጋው ሊታደገው አይችልም ” ሲሉም ተናግረዋል።
በመዲናዋ በመኪና አደጋ ግጭት ጭምር በየጊዜው የበርካቶች ሕይወት እንደሚያልፍ፣ በተለይ ዓይነ ስውራን ደግሞ ለዚህ ተጋላጭ እንደሆኑ ይነገራል፤ ጥናት አድርጋችሁ ነበር? ማኀበሩ ባለው መረጃ መሠረት ስንት ዓይነ ስውራን በዚሁ አደጋ ሞተዋል? ስንልም የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኀበርን ጠይቀናል።
የማበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ረታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ፣ ” የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች ሰብዓዊ መብቶች ቃል ኪዳን አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ዳታ ሊኖራቸው እንደሚገባ በመንግስታት ላይ ግልጽ የሆነ ግዴታ ይጥላል። ነገር ግን በመንግስት በኩል እንደዚህ አይነት የተደራጀ አሰራር የለም ” ብለዋል።
” እንደ ኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ከጥር 18 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ብዙ የመኪና ሞት አደጋዎች መድረሳቸውን ያለን መረጃ ያሳያል (ይህ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያጋጥሙትን የሚያካትት አይደለም)። አደጋው ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን ” ብለዋል።
” በጥር 18/2016 ዓ/ም አንድ የሞት አደጋ ሁለት ከባድ የአካል ጉዳት፣ በመጋቢት ለሚኩራ አንድ የሞት አደጋ ደርሶ ነበር፣ በሚያዚያ ወርም የሞት አደጋ ደርሷል፣ በመስከረም 2017 ዓ/ም በዓይነ ስውራን ላይ የሞት አደጋ ደርሷል፤ በሚያዚያ 2017 ዓ/ም በኮየ ፈጬ አንድ የሞት አደጋ ተመዝግቧል። አደጋው ከፍ እያለ እንደሆነ ነው የሚያሳየው ” ነው ያሉት።
የችግሩ ምክንያቶች ሁለት እንደሆኑ በጥናት መዳሰሱን ገልጸው፣ “አንደኛው የኢንፍራስትራክቸር ችግር፤ ሁለተኛ ደግሞ Unsafe የሆነ የአሽከርካሪዎች አነዳድ እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia


Leave a Reply