አጭር የፍ/ቤት ውሎ ሪፖርት


ቀደም ሲል የአፍንጮ በር ቤተ-መጽሃፍን በተመለከተ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ተብሎ የይግባኝ መልስ መስጠታችን ይታወሳል። ነገር ግን በመሃሉ ይግባኙ መልስ ሳያገኝ ቤተመጽሃፉ እንዲፈርስ መደረጉን ተከትሎ የክሱ ምክንያት ስለተቋረጠ የይግባኝ መዝገቡ እንዲዘጋልን ያመለከትን ሲሆን ያሁን ይግባኝ ባዮችም የመዝገቡን መዘጋት የተቃወሙ ሲሆን በመቃወሚያቸውም መልስ ሰጪዎች መዝገቡ ውሳኔ ካልተሰጠበት የቀድሞውን ውሳኔ ሊያንቀሳቅሱ ይችላሉ እንዲሁም ጉዳዩን በአስተዳደር ለመፍታት እየተነጋገርን ስለሆነ መዝገቡ ይዘጋ ቢባል እንኳን ለጊዜው ይዘጋልን በሚል ጠይቀዋል። በዛሬው ችሎትም ፍ/ቤቱ መዝገቡ ይዘጋ የሚለውን አልተቀበልነውም ነገር ግን መዝገቡ በጊዚያዊነት ተዘግቶ ይቆይ የሚለውን ተቀብለን መዝገቡ በጊዚያዊነት እንዲዘጋ መወሰኑን ከዳኛው ሰምተናል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content