ፈለገኪን 8ተኛ መድረክ ዕለተ ቅዳሜ ሚያዝያ 4 በማህበሩ ኣዳራሽ በድንቅ ሁኔታ ተከወነ። ማረፊያችን ቢሆን ሞቢሊቲ ላይ በፕሮግራሙ እንደሁሌው ዓይነስውራን ገጣሚያን፣ ደራሲያንና ድምጻዊያን፤ ከዓይናማ ወዳጆቻቸውጋር በመሆን መድረኩ ላይ ምርጥ ምርጥ ግጥሞቻቸውን መነባንባቸውን እና ወጎቻቸውን ኣቅርበዋል። ወጋገን ባንድም በጥዑመ ዜማዎች ኣድሞቆት ኣምሽቷል።
ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ የክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል ሲዘከር፣ ሁለገቡ የኪነጥበብ ሰው ታላቁ ከያኒ፣ ሃይሉ ጸጋዬ የእለቱ የክብር እንግዳችን ከመሆኑም ባሻገር ከሂወት ተሞክሮ ከማጋራቱም ከዓይነሥውራን ጋርም ያለውን ቁርኝት በድራማቹ ብቻ ሳይሆን ወገናዊነቱን የገለጸበት ንግግሩ በጣም የሚያስደት ከመሆኑም ተመልሶ እንደሚመጣ እና ለዓይነሥውራን ድራማ እንደሚሰራም ተናግሯል። እንዲሁም የብዙ አይነ ስውራንን ህይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን በማውጣት የሚታወቁት ጋሽ አማረ አስፋው በመካከላችን ብዙውን ኣባል ያስደሰተ እና ኩራት እንዲሰማው ኣድረገዋል። በኣደረጉት ንግግርም ዓይነሥውራን ራሳቸውን መቻል እንዳለባቸው እና ለዚህም መበርታት እንደሚገባቸው መክረዋል። ለማህበሩም ኣሳቢ እንዲሆኑ፣ መተባበር እንደሚኖርባቸው ኣስገንዝበዋል። ለሙሉ ዝግችቱ በማህበሩ የዩቲዩብ ቻናል በሚለቀቀው ቪዲዮ መከታተል ይቻላል። https://www.youtube.com/@enabtube1960
ታናናሾቻችንን እያጀገንን ታላላቆቻችንንም እንዲህ እናከብራለን።


Leave a Reply