እንደ ጎርጎሪሳዊያኑ አቆጣጠር ከአፕሪል 1-3 /2025 ድረስ ጂ አይ ዜድ- ለአካል ጉዳተኞች፤ ድርጅቶች ከሜይ 2023-ጁን 2025 ድረስ በሰሜን ኢትዮጲያ ጦርነት ወቅት በአማራና በአፋር ክልል በጾታዊ ጥቃት የተጎዱ ሴቶችን ለመደገፍ የተቀረጸናእየየተገበረ ባለው፤ ፕሮጀክት አማካኝነት ያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን፡፡ ጂ አይ ዜድን በተመለከተ በመክፈቻ ንግግር ወቅት በተደረገ ገለጻ ጂ አይ ዜድ-ይህንን ጨምሮ ከ70 በላይ ፕሮጀክቶችን በተለያዩ ፕሮግራሞች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተተገበረ እንደሚገኝ ገለጻ ተደርጎ ተቋሙን እንድናውቀው ሙከራ ተደርጓል፡፡ ይህንን ፕሮጀክት ለመቅረጽ ያነሳሳው ዋነኛ ምክንያት አካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ጦርነት መሰል በሆኑ ችግሮች፤ ወቅት ችግሮች ስለሚገጥማቸው በተለይም ደግሞ ሴቶች ከጾታዊ ትንኮሳ ባለፈ ተደራራቢ ችግሮች ስለሚገጥማቸው ለዚህ ችግር ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እንደነበር፤ ተነግሯል፡፡ በመቀጠል፡ የስልጠና ደንቦችና ህጎች ወጥተው፡ ራሳችንን፤ ከአቻዎቻችን ጋር ተዋውቀን፡ መልሰን የተዋወቅነው ሰው/ሴት ለታዳሚው እናድናስተዋውቅ ተደርጓል፡፡ ትውውቁ አይነስውራን ታሳቢ እንዲያደርግ ታስቦ ስለ፤ልብስና መሰል ጉዳዮች ሁሉ ገለጻ በማድረግ የተዋወቅን ሲሆን ወደ ቀኑ ማገባደጃ ላይ ስለ ልብስ፤ቁመት፤መልክና ሌሎች ማንነታዊ ጉዳዮችን ለተሳታፊ ማስተዋወቅ፤ ከሰብአዊ መብት አንጻር ተገቢ አይደለም የሚል እንቅስቃሴ በውጭው አለም፤ እየመጣ ነው ሲሉ አሰልጣኙ ሹክ ብለውናል፡፡
ራስን ከማስተዋወቅ ፡ቀጥሎ፤ የሰልጣኞችን እውቀትና አመለካከት፡ የቅድመ ስልጠና ጥያቄዎችን የሞላን ሲሆን በስልጠናው መጨረሻ እነዚሁኑ እንደምንጠየቅ ተነግሮን ወደ ዕለቱ ሰልጠና ከጠዋቱ፡ሻይ፤ዕረፍት መልስ ጀምረናል፡፡ ስልጠናው ሲጀምር አካል ጉዳተኛና አካል ጉዳተኝነትን ጽንሰ ሃሳቦችን ላይ ያለንን እውቀት ላይ ያተኮሩ ውይይቶችና በጥያቄና መልስ ስልጠና ሂደቶች ቀጥሏል፡፡ ቀጣዩ የስልጠና የትኩረት መስክ የአካል ጉዳተኞች መብት ሲሆን ተሳታፊዎች በ 3 ቡድን ተከፋፍለን
1. አለም አቀፍና ክፍለ አህጉራዊ ህጎችን
2. ሀገር አቀፍ ህጎች፤ደንቦች፤አዋጆችና መመሪያዎች
3. የተመድ የአካል ጉዳተኞች ቻርተን መርሆዎችን
በጋራ ውይይት አድርገን ያገኘነውን ሃሳብ ወደ እናት ቡድናችን ፤እየተመለስን ያስረዳን ሲሆን በጋራ የደረስንበትንም ጭብጥ ለታዳሚው በሙሉ አቅርበናል፡፡ በመጨረሻም ምንም እንኳ በርካታ ህጎች ደንቦች፤መመሪያዎችና አዋጆች ቢኖሩም ሁላችንም ማወቅ በሚገባን ልክና መልኩ አላወቅንም፡፡ አብዛኛው የማህበረሰባችንም ክፍልም አላወቃቸውም፡፡ በመሆኑም እንደ አካል ጉዳተኛ ማህበራት አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ከአለም አቀፍ እስከ ሀገር አቀፍ ድረስ ያሉትን ህጎች ደንቦች፤መመሪያዎችና አዋጆች ማሳወቅ የቤት ስራችን እንደሚሆን በመነጋገር የቡድን ስራው ሲያበቃ፡፡ በቀጣይ ኢንተርሴክሽናሊትስ በሚል ርዕስ ስልጠናው የተካሄደ ሲሆን አካል ጉዳት ኖሮባቸው፤ በሴትነታቸው ችግር የገጠማቸውን ልምድ እንዲያካፍሉ ሃሳብ ቀርቦ፤ ሁለት ሴቶች ለማቅረብ ፈቃደኛ ሆነው፡ አንደኛዋ ሴት ተሳታፊ እርሳቸው በቅርበት በሚያውቁዋት ሴት አይነስውር ላይ የተደረገውን አስገድዶ የመድፈርና ከዚያ በሁዋላ የመጡ ችግሮችን ያጋሩ ሲሆን ሌላኛዋ ተሳታፊ ለነገ ጠዋት በመቅጠር ቀን አንድ ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡

Leave a Reply