የስልጠና ተሳትፎ የ2ኛ ቀን ውሎ አጭር ዘገባ


ዛሬም ላም በረት ኃይሌ ግርንድ ሆቴል ነኝ፡፡ 2ኛ ቀኔ፡፡ ዳገታማ የሆነውን የሆቴል መግቢያ በር አቋርጬ 34 ደረጃዎችን ከወጣሁ ነበር ጭላሎ በሚባለው ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ለ 2ኛ ቀን ስልጠና 30 ደቂቃ ቀድሜ መገኘት ችዬ ነበር፡፡ ከሠላምታ በመቀጠል የመጀመሪያ፤ የቀን ውሎ ምን እንደሚመስል አጭር ለሆኑ ደቂቃዎች ክለሳ ከተደረገ በሁዋላ ትላንት ሴት አካል ጉዳተኛ የሆኑና በሴትነታቸው የገጠማቸውን ልምድ እንዲያገሩ፤የተዘጋጁት፤ልምዳቸውን አጋርተውን ወደ ዕለቱ ስልጠና ገብተናል፡፡
የዕለቱ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና የተጀመረው ተሳታፎዎች በቡድን ተከፋፍለን ጾታዊ ጥቃትን ፤ ትርጉም እንድንሰጥ፤፤ የጾታዊ ጥቃት አይነቶችን፤ እንድንዘረዝርና የእያንዳንዱን ትርጉም እንድንሰጥ የተደረገ ሲሆን ቡድኖች በመከፋፈል ከትርጉም ባለፈ እያንዳንዱን ጽንሰ ሃሳብ፤ በአልጣኟ ተጨማሪ የስልጠና ስላይዶች በመታገዝ፤ በዝርዝር አይተነዋል፡፡ ይህ በመሆኑም አብዛኛው ተሳታፊ በጉዳዩ ላይ ያለው እይታና እውቀት እንዲዳብር አስተዋጽኦ አደርጓል፡፡
ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአንዲት አካል ጉዳተኛና ባለትዳር የሆነች እንስት በትዳር አጋርዋ የደረሰባትን፤የቤት ውስጥ ጉዳቶች በጹሑፍ እንደመወያያ ተሰጥቶን እርሱን አንብበን የደረሱባትን ጥቃቶች በፊት ከተማረንው የጾታዊ ጥቃቶች አንጻር በየትኛው በኩል እንደሚመደብ፤ ምልክቶችን ጭምር እንድናስቀምጥ በመደረጉ ግንዛቤያችን ከፍ እንዲል አደርጎታል፡፡
ከምሳ መልስ በነበረን ውሎ የምናውቀው አንድ አካባቢ መርጠን በካርታ እንድናሳይ የተጠየቀን፤ ሲሆን፤ በየቡድናችን የፈለግነው አካባቢ መርጠን የሳል ሲሆን አብዛኞቻችን ግን በካርታ ያሳየናቸው አካባቢዎች አካል ጉዳተኞችን ቢሮዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነበር፡፡ በዚህም ረገድ አንድ ቡድን ማህበራችንን የካቲት ሆስፒታል ጉን ዋናው መንገድ ላይ አውጥቶ በማፑላይ ያሳየ ሲሆን ምነው ብዬ ለጠየቅሁት ጥያቄ ኢናብ ዋናው መንገድ ላይ ወጥቶ መታየት አለበት ስለምናስብ ነው የሚል ፈገግ የሚያስብል መልስ ቢሰጡም በስህተታቸው ግን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በመቀጠል የሰራናውን ካርታ በማስመልከት፤ የትኞቹ ቦታዎች ለጾታዊ ጥቃት መጋለጥ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፤ ጥቃት የደረሰባቸው አካላት፤ የተለያዩ ግልጋሎቶችን ቢጠይቁ ማግኘት የሚችሉባቸው፤ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስለመኖራቸው፤ቦታዎቹ ለአካል ጉዳተኞ ምቹ ስለመሆን አለመሆናቸውን በሰራነው ካርታ ላይ እንድናስቀምጥ የተጠየቅን ሲሆን፤ ሁሉም ተሳታፊ ይሆናሉ ያላቸውን ምላሾቻችንን በካርታው ላይ አስቀምጠን ቡድኖች ካርታዎችን በተሰቀሉበት ግድግዳዎች ላይ እዞሩ ገለጻ እየተደረገላቸው የዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቋል፡
በመጨረሻም የስልጠናው ጊዜ አለም አቅፍና ክፍለ አህጉራዊ ህጎችን እና አገራዊ ህጎቶችን ያለባቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት ክፍሉ በአራት ቡድን ተከፍሎ በአምሳለ ፍርድ ቤት ዳኞች ተሰይመው ክርክር ተደርጎ፤ ማጠቃለያውን አሰልጣኝዋ በሁሉም ህጎቶች ያሉትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በስላይድ አቅርበውልን የዕለቱ ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡
የቀን ሁለት፤ ውሎ ተፈጸመ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content