የኢትዮጵያ ዓይነሥውራን ብሔራዊ ማኅበር 17ተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ 3ተኛ መደበኛ ስብሰባውን መጋቢት 27-28 2017 ዓ.ም. በናዝሬት ከተማ አካሄደ።
በማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ በየዓመቱ በቦርዱ እና የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በተገኙበት በሚቀረጹ አጀንዳዎችን እና ከ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በሚነሱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ የሚሰጥበት ነው። በዘንድው አመትም ጠቅላላ ጉባኤውበተለያዩ ኣጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን የስተላለፈ ሲሆን አጀንዳዎቹም፡
1. የ2024 የስራ ክንውን ሪፖርት ማቅረብ
2. የ2024 የውጪ ኦዲት ሪፖርት ማቅርብ
3. የ2025 አመታዊ እቅድ ማቅረብ
4. መተዳደሪያ ደንብ አጀንዳ ማንበብ
5. የማህበሩ የጠቅላላ ጉበዔ አባል የሆኑት አቶ ኩማ አሊን በተመለከተ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ማፀደቅ
6. የማህበሩ ቦርድ የንግድ ስራ ድርጀት እንድቋቋም ጠቅላላ ጉበኤ ውክልና እንዲሰጠው የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ማፀደቅ
7. የማህበሩ ቦርድ ተባባሪ አባላትን ለመምረጥ እንዲችሉ ከጠቅላላ ጉባዔ ውክልና እንዲሰጠው የውሳኔ ሐሳብ ማፀደቅ
የማህበሩ 2024 በጀት ዘመን የክንውን ሪፖርት በማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ በዳሶ እንዳለ የቀረበ ሲሆን ከሳቸው ቀጥሎም በማህበሩ የውጭ ኦዲተር ዓለም ኣቀፍ የኦዲት ደረጃዎችን በመከተል ኦዲት መደረጉን እና በሲቢል ማህበራት በወጡት መመሪያዎችም ጠብቀው መስራታቸውን ኣሳውቀው በውጤቱም ላይ አስተያየት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በቀረቡት ሪፖርቶች ሁለቱም ሪፖርቶች ላይ በርካታ ጥያቀዎችና ኃሳቦች ከቤቱ ቀርበው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ከተሰጣቸው በሁዋላ ሪፖርቶጩ በአብላጭ ድምፅ ፀድቀዋል፡፡
ቀጥሎም የ2025 በጀት ዘመን ዕቅድ በማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ቀርቦ ጥያቄዎችና አስተያያቶች ተጨምረውበት በተሰጡት አስተያያቶች ዳብሮ የማህበሩ 2025 በጅት አመት እቅድ እንዲሆነ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡
በቀጣይ የማህበሩን የደንብ ማሻሻያ ለውይይት ለማቅረብ የድጋፍ ሞሽን እንዲሰጥበት ተደርጎ በድንቡ መሰረት ተፈላጊውን የሞሽን ድጋፍ ስላገኘ ለውይይት ቀርቦ የተሻሻለው ረቂቅ በንባብ ተሰምቷል፡፡በቀረበው ማሻሻያ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ ኃሳብ ሰጥተውበት፤ አሁን ይጸደቅ ወይስ ቦርዱ አይቶ የተሰጠውን ግብአት ተጠቅሞ እነደገና ይስራው በሚለው ላይ ድምጽ ተሰጥቶበት ቦርዱ ተመልሶ እንደገና ይስራው የሚለው ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ አልፏል።
በ17ተኛ ዙር አባል የሆኑት ኣቶ ኩማ ዓሊ ከማህበሩ ጋር መስራት እንደማይፈልጉ ባሳወቁት ጉዳይ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎ፤በማህበሩ ደንብ እና ህግ መሰረት ይነሱ በሚለው በአብላጭ ድምጽ ውሳኔ ተሰጥቶ አቶ ኩማ ዓሊ ታግደዋል።
የመጨራሻው በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ኣንቀጽ 38 ንዑስ 3 መሰረት ማህበሩ በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚፈቅድ በመሆኑ፡ በደንቡ አንቀጽ 14 መሰረት የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣን መሰረት ለቦርዱ ውክልና እንዲሰጥ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለቦርዱ ውክልና ለመስጠት የሚለውን አማራጭ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።
በመጨረሻም የሲቢል ማህበረሰብ ባለስልጣን ተወካይ የሆኑት አቶ ይታያል በላቸው የመዝጊያ ንግግር ኣድርገዋል። በንግግራቸውም የነበረው ጉባዔ በጣም ዲሲፕሊን የነበረው እና ሃሳብን በሃሳብ የማንሳት እና የመጣል ተግባራዊ የሆነበት እንደሆነ ጠቅሰው በውጤቱም መደሰታቸው እና ጥሩ ተሞኩሮ እንደቀሰሙ ገልጸዋል። ስብሰባውም ለተሰታፊዎች ምስጋናና የመልካም ጉዞ መልዕክት ተላላፎ፤ የጉባዔው ፍጻሜ ሆኗል።


Leave a Reply