የተስፋችን ብስራት፣ በመክሊታችን ኩራት። እነሆ፣ ዓይነስውራን እና የዓይነስውራን ወዳጆች በተለየ የስነ-ጽሁፍ፣ የሙዚቃና መሰል የኪነጥበብ ስራዎች በወጋገን ባንድ ታጅበው የሚደምቁበት አሥራ አንደኛው የፈለገኪን የኪነጥበብ መድረክ ደማቅ በሆነ ዝግጅት ተከናወነ። መሰናዶውም በ ማርታ ነጋሽ እና በኢሳያስ ባንጫ አጋፋሪነት ተመርቷል።
ገጣሚና ደራሲ ስንዱ ገብሩ ተዘክራበት፣ ተወዳጇ ደራሲ ህይወት እምሻው የክብር እንግዳ የሆነችበት ሃሳቧን እና የህይወት ልምዷን አጋርታበት ኣባላቱ ደሥሥሥ የሚል ጊዜ አለፈ።
ታናናሾቻችንን እያጀገንን ታላላቆቻችንንም እንዲሁ እናከብራለን ሞቶኣችን ሆኖ፥ ፈለገኪን፣ ስድስት ኪሎ በኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሔራዊ ማኅበር ግቢ ሀምሌ 5 ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ተመደረከ።


Leave a Reply