ለአይደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በአካቶ ትምህርት ዙሪያ የ2 ቀናት ስልጠና ተሰጠ።


ስልጠናው የተሰጠው በመቀሌ ከተማ ዘማሪያስ ሆቴል ሲሆን የተሰጠበት ቀን ሀምሌ 15 እና 16 2017 አ.ም ነው።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የትምህርት ቤቱ መምህራን ለአካል ጉዳተኞች በተለይም ለአይነ ስውራን ከዚያም አልፎ ለሁሉም ተማሪዎች ምቹ የሆነ የትምህርት አሰጣጥ ስነ ዘዴን እንዲያውቁና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው።
39 ግለሰቦች ስልጠናውን የተከታተሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሰላሳ አምስቱ የአይደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን፣ ሁለቱ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ ባለስልጣናት እና 2 የማህበራችን ተወካዮች ናቸው። እነዚህ ተሳታፊዎች በትምህርት ቤቱ እና በክልል ደረጃ አካቶ ትምህርትን በመተግበር እና በመደገፍ ያላቸው ቀጥተኛ ሚና ታሳቢ ተደርጎ የተመረጡ ናቸው።
የስልጠናው ይዘት የአካቶ ትምህርት ጽንሰ ሀሳብን፣ የክፍል አስተዳደርን፣ የማስተማር ስነ ዘዴን፣ የምዘና ስልቶችን፣ ለይቶ የማስተማር ስነዘዴን (differentiation)፣ የግል ፈጠራንና የመሳሰሉትን ያካተተ ነበር።
የቡድን ውይይቶች፣ የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጦች፣ ጥያቄና መልስ፣ ስእሎች፣ ድምጾችና ቪዲዮዎች አሰልጣኙ የተጠቀመባቸው የማሰልጠኛ ስልቶች ናቸው።
ተሳታፊዎች ስልጠናው ስለ አካቶ ትምህርት የነበራቸውን ግንዛቤ ማሳደጉን ገልጸው በስልጠናው ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉትን ተግባራዊ ስልቶች አድንቀዋል። ብዙ መምህራን የተማሩትን በክፍላቸው ውስጥ ለመተግበር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸው ተጨማሪ የክትትል ስልጠና ወይም የድጋፍ ቁሳቁሶች እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።
የትምህርት ቢሮ ባለስልጣናት እንደነዚህ ያሉ ስልጠናዎችን በሌሎች ትምህርት ቤቶች መድገም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በአስተዳደር ደረጃ ሁሉን አቀፍ ልምዶችን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
በአጠቃላይ ስልጠናው በአይደር ትምህርት ቤት የተሟላ የአካቶ ትምህርት ስርአት እንዲዘረጋ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የመጀመሪያዋን ጠጠር ወርውሯል። ተሳታፊዎች በንቃት የተሳተፉ ሲሆን የስልጠናው ጭብጥም በመምህራኑ ዘንድ በጥሩ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቷል።
በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ማህበሩ ለስልጠናው ተግባራዊነት የራሱን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግና ፕሮጀክቱ እና ስልጠናው በክልሉ ውስጥ ወደ ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም እንዲሰፋ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content