የኪነ ጥበብ መብራት የምትበራበት በኩራት፣ ዓይነስውራንና የዓይነስውራን ወዳጆች በተለየ የስነጽሁፍ፣ የሙዚቃ ድግስ
የኪነ ጥበብ መብራት የምትበራበት በኩራት፣ ዓይነስውራንና የዓይነስውራን ወዳጆች በተለየ የስነጽሁፍ፣ የሙዚቃና መሰል የኪነጥበብ ስራዎች በወጋገን ባንድ ታጅበው የደመቁበት 10ኛው የፈለገኪን የኪነጥበብ መድረክ ቅዳሜ ግንቦት 30 ከሰዓት በኋላ ተመደረከ።
በዝግጅቱም የእለቱ ተዘካሪ በተለያዩ ታላላቅ ድርሰቶቻቸው በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ የስነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ታላቅ እመርታ ያስመዘገበው ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘውን ልብወለድ የደረሱት ታላቁ ደራሲ የክብር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ ነበሩ። ታላቅ ደራሲ በተለይም ሰመመን በተሰኘው ልብ ወለድ ከልባችን የማይጠፋው ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ ተጋባዥ እንግዳችን ሆነዋል። እንዲሁም የማህበራችን ፕረዚደንት ኣቶ ኣበራ ረታ እና ጋሽ ገብሬም ዝግጅቱን ተሳትፈዋል።
“ታናናሾቻችንን እያጀገንን ታላላቆቻችንንም እንዲህ እናከብራለን።” ፈለገኪን ለጥበብ ርሃብተኞች የእርካታ ምንጭ ለመሆን፣ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በኢትዮጲያ አይነስውራን ብሄራዊ ማህበር ዋና ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በየወሩ ይከሰታል። እዚያው እንገናኝ።

Leave a Reply