በሰባት ቅርንጫፎች በጋራ የአድቮኬሲ (ውትወታ) ስራ ዙርያ በቅርንጫፎቹ ከሚገኙ የአካል ጉዳትኛ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት ተደረገ።


 

በራይዝ ፕሮግራም በታቀፉ ሰባት ቅርንጫፎች ማለትም በደሴ፣ በጎንደር፣ በደብረብርሃን፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሰበታ፣ በሃዋሳና በመቀሌ ቅርንጫፎች በጋራ የአድቮኬሲ (ውትወታ) ስራ ዙርያ በየቅርንጫፎቹ ከሚገኙ የአካል ጉዳትኛ ማህበራት ተወካዮች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት ተደረገ።
የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ለጋራ ችግሮች በጋራ መፍትሄ ለማምጣት፣ በቅርንጫፍ ደረጃ የሚደረጉ የውትወታ ስራዎች ወጥነት ባለው መልኩ ሁሉንም ማህበራት በማሳተፍ ሊሰራ የሚችልበትን ሂደት ለመወያየትና በየጊዜው በማህበራት መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት በማሰብ ነው።
ይህ መድረክ በየቅርንጫፉ የኮሚቴ ሰብሳቢዎች የተመራ ሲሆን ከእንቅስቃሴ ጉዳት ማህበር፣ ከመስማት የተሳናቸው ማህበር፣ ከሴት ኣካል ጉዳተኞች ማህበር፣ ከክልል አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽንና የተለያዩ አካል ጉዳተኞች ላይ የሚሰሩ ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
ተሳታፊዎቹ አስቸኳይ እና በቅድምያ ሊቀረፉ ይገባል ያሏቸውን ተግዳሮቶች የመለየት ስራ የሰሩ ሲሆን ከዛም ጋር ተያይዞ በርከት ያሉ ሃሳቦችን ተለዋውጠዋል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ከዚህም ቀደም በጋራ የተሰሩ ስራዎችን እንደማሳያ በመጥቀስ ይህን የበለጠ ተቀራርቦ የመስራት ጥያቄ ተገቢ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በአካል ጉዳትኞች ላይ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች በጋራ ካልሆነ ለየብቻ በሚሰሩ ውትወታዎች ሊቀረፉ እንደማይችሉ አክለው፣ ይህን የመሳሰሉ የጋራ መድረኮች ቀጣይነት ባለው መልኩ ቢዘጋጅ የበለጠ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት የነበረውን ተሳትፎ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ቀጥሎ ተያይዘዋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content