በ6 ቅርንጫፎች ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የእንቅስቃሴና የአካባባቢ ትውውቅ (Orientation and Mobility) ስልጠና ተጠናቀቀ።


በዴንማርክ ዓይነስውራን ማህበር ድጋፍ በመተግበር ላይ ባለው የራይዝ ፕሮግራም አማካኘነት በ6 ቅርንጫፎች ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የእንቅስቃሴና የአካባባቢ ትውውቅ (Orientation and Mobility) ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናው በደሴ፣ በጎንደር፣ በደብረብርሃን፣ በሃዋሳ፣ በመቀሌና በሰበታ ቅርጫፎች ለሚገኙ 60 አባላት የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ይዘት በመጠኑ ቢለያይም መሰረታዊ የሚባሉ የእንቅስቃሴና የአካባባቢ ትውውቅ ክህሎቶች ላይ ያተኮረ ነበር። እነዚህም፣ ሌሎች ህዋሳቶችን በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን መለየት፣ የወደቀ ነገርን በጥንቃቄ ፈልጎ ማግኘት፣ የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ በጠባብ እና በኣስቸጋሪ መንገድ የሚደረግ እንቅስቃሴ፣ ደረጃ ወውጣት መውረድ፣ ከረዳት ጋር የሚደረግ እንቅስቃሴ፣ መንገድ ማቋረት፣ በመጨረሻም ቀለል ያለ የነጭ በትር ወይም ኬን ኬን ጥገና ልምምድ ኣድርገዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በእንቅስቃሴ እና በኬን ኣጠቃቀም ዙርያ የተሻለ እውቀት እንዳገኙ እና በራስ መተማመናቸውን እንዳሳደገላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ከስልጠናው ጋር የትሰጣቸው ነጭ በትር ደሞ የበለጠ በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ እንደሚያግዛችው ገልጸዋል።
የየቅርንጫፉ የኮሚቴ አባላትን፣ አስተባባሪዎችን፣ ስልጠናውን የሰጡ አሰልጣኞችን እና ለስልጠናው መሳካት የተባበሩንን ሁሉ እያመሰገንን የስልጠናውን ሂደት የሚያሳዩ ምስሎችን ከታች አያይዘናል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content