የኢትዮጵያ ዐይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር የብሬል ቀንን እና የፈለገ-ኪን መርሀ ግብርን በድምቀት አከበረ


አዲስ አበባ – ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ዐይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር (ENAB) ቅዳሜ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ዓመታዊውን የብሬል ቀን እና የ”ፈለገ-ኪን” የኪነ-ጥበብ መርሀ ግብርን በልዩ ድምቀት አክብሮ አሳለፏል።

በማህበሩ ዋና ጽህፈት ቤት በተካሄደው በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ረታ፣ የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች እንዲሁም በርካታ የማህበሩ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የዕለቱን መርሀ ግብር ልዩ ካደረጉት ክስተቶች መካከል የክብር እንግዶች ተሳትፎ ይጠቀሳል። በተለይም በኢትዮጵያ የፊልምና የቲያትር ዘርፍ ትልቅ አሻራ ያሳረፉት አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ኪሮስ ኃይለሥላሴ በቦታው ተገኝተው ለታዳሚው የሞራል ድጋፍ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በሃይማኖታዊ ትምህርቶቻቸው እና በተወዳጅ አንደበታቸው የሚታወቁት መምህር እና የቲዎሎጂ ሊቅ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት፣ ለታዳሚው በሚያቀርቡት ጥልቅ ምክር እና አስተማሪ መልዕክት ፕሮግራሙን አድምቀውታል።

መርሀ ግብሩ የብሬል ጽሁፍ ለዐይነ ስውራን ትምህርት እና የመረጃ ተደራሽነት ያለውን ወሳኝ ሚና በተመለከተ ግንዛቤ የተፈጠረበት ሲሆን፣ በፈለገ-ኪን የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶችም ታጅቦ እጅግ አዝናኝ እና አስተማሪ በሆነ መልኩ ተጠናቋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content