የየካቲት 12 ሆስፒታል የሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም በጠራው ስብሰባ ላይ መገኘት


ዛሬ ሐሙስ ሚያዚያ 2 2017 ዓ.ም የየካቲት 12 ሆስፒታል የሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም በጠራው ስብሰባ ላይ መገኘት ተችሏል፡፡ ስብሰባው የተካሄደበት ቦታ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ሲሆን ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጠው ሊፍት በመበላሸቱና ቀሪ አንድ ሊፍት ቢኖርም ለህመምተኞች ሲባል አገልግሎት ስለማይሰጥ እያንዳንዳቸው 23 ደረጃ ያላቸውን ሰባቱን ፎቅ መውጣት ግዴታ ነበር፡፡ ለስብሰባው የተያዘው አዳራሽም የጠዋት ስብሰባ በሚያደርጉ ሌሎች አካላት ተይዞ ስለነበር በማቆያ አዳራሽ ውስጥ ቆይቶ የማለዳው ተሰብሳቢዎች ከለቀቁ በኋላ መግባት ግድ ሆኗል፡፡
በማንኛውም ስብሰባ እንደሚደረገው የስብሰባዉ አዘጋጆችና የሆስፒታሉ ዋና ኃላፊ በየተራ ንግግር አድረገው አራት ሰዎች የተለያዩ ሪፖርቶችን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ አብዛኛው ተሳታፊ ሆስፒታሉ በአገልግሎቱ እየተሻሻለ መሔዱን በመግለፅ አመስግነዋል፡፡
በማህበራችን በኩል speech therapy በእይታ የሚሰጠ ህክምና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለአይነስውራን አገልግሎት እንደማይሰጥ በመጥቀስ ይህ ተገቢ ባለመሆኑ 1. አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎቹ የራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም እንዲያገለግሉ ማድረግ፤ 2. ለአይነስውራን ተደራሽ በሆነ መንገድ ህክምናውን መስጠት የሚያስችሉ መሳሪያዎች በውጪ ሀገር ስለሚገኙ በቂ በጀት መድቦ መሳሪያዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረግ እንዳለበት ተገልጿል፡፡ ኃላፊዎቹም መረጃዉ እንዳልነበራቸው ጠቅሰው ከባለሙያዎቹ ጋር በመነጋገር ባስቸኳይ መፍተሄ ለመስጠት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content