ፈለገኪን 9ኛ መድረክ ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 2 በማህበሩ ኣዳራሽ በድንቅ ሁኔታ ተከወነ።


ተስፋችን በአንድነታችን እንዲሰምር፣ አሁንም ሰላምን እንዘምር። ደግሞም በመገናኘታችን፣ እልፍ ነው በረከታችን። የተስፋችን ማስፊያው የበረከታችን ጌጥ፣ ፈለገኪን ሆኖ በወርሃ ግንቦት በኢናብ ቤት፣ በሁለተኛው ቀን በዕለተ ቅዳሜ፣ ማረፊያችን ሆኖ ሞቢሊቲ ላይ: ያኔ- ጉዳያችን ኪነት፣ ነገራችን ጥበብ ሆኗል። ምክኒያቱም፣ ቀኑ የዘጠነኛው የፈለገኪን የኪነጥበብ መድረክ። በፕሮግራሙ እንደሁሌው ዓይነሥውራን ገጣሚያን፣ ደራሲያንና ድምጻውያን፤ ከዓይናማ ወዳጆቻቸው ጋር በመሆን መድረኩ ላይ በወጋገን ባንድ ታጅበው ነገሱበት።
ደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማ በተዘከርበት የፈለገኪን መድረክ፣ ደራሲና ከያኒ ውድነህ ክፍሌና የክብር እንግዳችን ሆኗል።
ስድስት ኪሎ በኢትዮጲያ ዓይነሥውራን ብሄራዊ ማህበር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በየወሩ እንከሰታለ።

ለሙሉ ዝግችቱ በማህበሩ የዩቲዩብ ቻናል በሚለቀቀው ቪዲዮ መከታተል ይቻላል። https://www.youtube.com/@enabtube1960
ታናናሾቻችንን እያጀገንን ታላላቆቻችንንም እንዲህ እናከብራለን።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content