የ 2ኛ ዓመት ፈለገ ኪን አምስተኛ መድረክ


የተስፋችን ብስራት፣ በመክሊታችን ኩራት። እነሆ ፈለገኪን ቀጥሏል። የሁለተኛ ኣመቱ ጉዞ አምስተኛ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ ጥር ሰላሳ ቀን በልዩ ሁኔታ ይመደረካል። በዚህ የኪነጥበብ ድግስ ጸሃፈተውኔትና ደራሲ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ በክብር የሚዘከሩ ይሆናል። ተወዳጁ አርቲስት ኪሮስ ኃይለስላሴና አንደበተ ርቱእ መምህር መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ደግሞ የፕሮግራሙ ልዩ እንግዶች ሆነው መሃላችን ይገኛሉ።
ከዚህም በተጨማሪ የእስሌትና እስታይለስ ብእረኞች የብሬል ቀንን አስመልክቶ በብሬል ስለ ብሬል በእስታይለሶቻቸው የወጉትን ጥኡም ወግ ያወጉናል። እንደቀደሙቱ የፈለገኪን መድረኮች ሁሉ አይነስውራን የኪነጥበብ ባለተሰጥኦችም ከአይናማ ወዳጆቻቸውጋ በወጋገን ባንድ ታጅበው መድረኩን ያደምቁታል። የማህበሩ ሰራተኞች የፕሮግራሙን ሂደት ለማሳለጥ አደግድገው ይቆማሉ። አዎ። ታናናሾቻችንን እያጀገንን ታላላቆቻችንን እንዲህ እናከብራለን። ተስፋችን በአንድነታችን እንዲሰምር፣ በጋራ ሰላምን እንድንዘምር፣ ጥር ሠላሣ እለተቅዳሜ ስምንት ሰአት 6 ኪሎ የኢትዮጲያ ኣይነስውራን ብሄራዊ ማህበር ግቢ። (ሞቢሊቲ) የቀጠሯችን መፈጸሚያ ይሁን።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content