ቀደም ሲል ተሻሽሎ በሥራ ላይ በነበረው የባንክ ሥራ አዋጅ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽ የባንክ አገልግሎት የማግኘት መብትን ባጣበበ መልኩ የተቀረጸ አንቀጽ በመያዙ ምክንያት ባንኮች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽና ምቹ አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማድረጉም በላይ ብሔራዊ ባንክ በጉዳዩ ላይ መመሪያ እንዳያወጣ መመሪያ የማውጣት መብቱን ሙሉለሙሉ ለብሔራዊ ባንኩ በመስጠት ‘አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው’ መመሪያ ያወጣል በሚል የተቀመጠ ስለሆነ ባንኩ በተደጋጋሚ መመሪያ እንዲያወጣ ሲጠየቅ የቆየ ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ ሳይገኝ ቀርቷል።
ለረጅም ዓመታት የማኅበሩ የአድቮኬሲ አጀንዳ ሆኖ የቆየው ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የባንክ አገልግሎት የማግኘት ጉዳይ በአዲሱ አዋጅ እንደሚከተለው ተሻሽሏል:
አንቀጽ 81 የባንክ አገልግሎቶችን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽና ምቹ ስለማድረግ
- ማንኛውም ባንክ ለአካል ጉዳተኛ ደንበኞች ተደራሽ እና ምቹ የባንክ አገልግሎት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ብሔራዊ ባንክ የባንክ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና ምቹ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መመሪያ ያወጣል
ይህን ስኬት የኔ ብሎ (own በማድረግ) በሚዲያም ሆነ (በማኅበሩ ድህረ-ገጽ እና ሌሎች ማሕበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ)፣ ለለጋሾች፣ እንዲሁም በፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል የመጻፍና የማመልከት ተግባራት ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ብንጠቅሰው ጠቃሚ ይሆናል።
ስኬቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ ላይ በተቀመጠው መሰረት መመሪያ እንዲወጣ መጠየቅ፣ እንዲሁም የሚወጣው መመሪያ በተጨባጭ የዓይነስውራንን ተደራሽ የባንክ አገልግሎት የማግኘት ችግሮችን የሚፈታ እንዲሆን ተከታትሎ ውትወታ የማድረግ ሥራ የሚጠበቅብን ሲሆን፣ ከዓይነስውራን ከቼክ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ላይም ለመፍትሄው መሥራት ይጠበቅብናል።
አዋጁ እዚህ ተያይዟል!

Leave a Reply