የ5 ቀናት የብሬል ስልጠና ተሰጠ


 

ከሰኔ 20 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ 5 ቀናት፣ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የማህበሩ አዳራሽ ለ24 በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ዓይነስውራን ተማሪዎች የብሬል ዕውቀት ማሻሻያ ስልጠና ተሰጥቷል። የስልጠናው ተሳታፊዎች ጀማሪዎች እንዲውን የተወሰነ የብሬል እውቀት ቢኖራቸዉም በተለያዩ ምክንያቶች ብሬልን ሳይጠቀሙ የቆዩና ክህሎታቸው እየቀነሰ የመጣ ይገኙበታል።
የስልጠናው ይዘት ከመሰረታዊ የብሬል አመጣጥ ጀምሮ፣ የብሬል ፊደላት አጻጻፍ (Braille Alphabet)፣ ቃላት አወቃቀር፣ በመጨረሻም የብሬል ማሳጠርያዎች (contractions) ላይ የተኮረ ነበር።
ስልጠናው በርካታ የረሷቸውን ማሳጠትያዎች እንዳስታወሳቸው እና የበለጠ ለማንበብና ብሬልን ለመጠቀም እንዳነሳሳቸው፣ ከዚህ በፊት በድምጽ ቅጂ በመታገዝ ሲማሩ እንደነበር እና ካሁን በኋላ የብሬል ማስታወሻዎችን በማዘጋጀት፣ የብሬል መጽሃፍትን በማንበብ የትምህርት ውጤታቸውን ለማሻሻል እንደሚጥሩ ገልጸዋል። እንደዚህ አይነት ስልጠና ተጠናክሮ መቀጠል አንዳለበትም አሳስበዋል።
በመጨመርያም ስልየናውን ለሰጠችልን መምህርት አታላይ አበባውን እያመሰገንን በስልጠናው ወቅት የተነሱ ተማሪዎች በልምምድ ላይ ሳሉ የሚያሳይ ፎቶዎች ከዚህ በታች ተያይዘዋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Skip to content