የተስፋችን ብስራት፣ በመክሊታችን ኩራት!
የ”ፈለገ-ኪን” የኪነ-ጥበብ መድረክ የሁለተኛ ዓመት ጉዞውን ስድስተኛ መድረክ ሊያካሂድ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የፊታችን ቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከናወነው ይህ የጥበብ ድግስ፣ በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውንና በቅጽል ስሙ “ገሞራው” በመባል የሚታወቀውን ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስን በክብር የሚዘክር ይሆናል።
የክብር እንግዶቻችን
በዚህ ልዩ መርሃ-ግብር ላይ በታሪካዊው የተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት በነበራቸው ተሳትፎ የሚታወቁና ሀገራቸውን በአምባሳደርነት ያገለገሉት ደራሲና አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል እንዲሁም በ”ዮቶር” እና መሰል ድንቅ ድርሰቶቹ የሚታወቀው የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ በክብር እንግድነት ይገኛሉ። በተጨማሪም የባለቅኔው ገሞራው የቅርብ ቤተሰቦችና የትግል ጓደኞች በመድረኩ የሚሰየሙ ይሆናል።
ጥበብና አንድነት
እንደ ሁልጊዜው ሁሉ፣ የዓይነስውራን የኪነ-ጥበብ ባለተሰጥኦዎች ከአይናማ ወዳጆቻቸው ጋር በመሆን በወጋገን ባንድ ታጅበው መድረኩን በሙዚቃና በግጥም ያደምቁታል። ታናናሾቻችንን እያበረታታን፣ ታላላቆቻችንን እያከበርን የተስፋና የሰላም መዝሙርን በጋራ እንዘምራለን።
የቀጠሮ መረጃ፦
- ቀን፦ ቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
- ሰዓት፦ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ
- ቦታ፦ 6 ኪሎ፣ የኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሔራዊ ማኅበር ግቢ (ሞቢሊቲ)



Leave a Reply