
ለአይነ-ስውራን የፋይናንስ ተደራሽነትና ዲጂታል ባንክ ተጠቃሚነት ላይ በባህዳር ከተማ የአንድ ቀን ስልጠና 23 ለሚሆኑ ከተለያዩ ባንኮች ለመጡ ተሳታፊዎች በቀን 25/10/2017 አ.ም ተሰጥቷል።
የስልጠናው ይዘት :
በባንክ አገልግሎት ተደራሽነትና የድጀታል የባንክ አቅርቦት ላይ ያተኮረ በተለይም የአይነ-ስውራን አባላት በዘርፉ ያጋጠማቸውን ዋና ችግሮች፥ ምቹ ሁኔታ እና አገልግሎት አካታችነት ክፖሊሲና በባንክ ተቋማት ከሚታየው ትግበራ አንጻር ስልጠናው ተሰጥቷል። ይህ ስልጠና በባ/ዳር ከተማ የሚገኙ ሁሉንም ባንኮች ያካተተ ሲሆን አብዛኛቹ ባንኮችም ተገኝተዋል። በስልጠናው ዘርዘር ባለ መልኩ የፋይናንስ ነክ ህጎችን፣ የአፈፃፀም ደረጃቸውን፣ ተግዳሮቶችን እና ዓይነ-ስውራንን በቀላሉ ተካታች የሚሆኑበት ሁኔታ ለምፍጠር የዘርፉ ተቋማትን ግንዛቤ በማጎልበት እና አቅም በመገንባት የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎቶት ተደራሽነትን ማሳደግ እንዲቻል ገንዛቤ ተፈጥሯል።
ስልጠናውን የENAB ባ/ዳር ቅርንጫፍ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ያሬድ ደስታው በሰጡት የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በባንክ ዘርፉ ዓይነ-ስውራን የገጠሟቸውን ፈተናዎች፣ በዲጂታል አጠቃቀም ረገድ ያለውን ውስንነት፣ ሊደረጉ የሚችሉ አወንታዊ እድሎችን እንዲሁም ለዓይነ-ስውራን የገንዘብ ብድር ተደራሽነት የሚሉ ጉዳዮችን አንስተዋል ። በመቀጠል የENAB የኢኮኖሚክ ልማት አስተባባሪ ለተሳታፊዎቹ ስለ ማሀብሩ ታሪካዊ ዳራና የካዲር ፕሮጀክት የታቀዱ ስራዎች እና ዋና ዋና ተግብራት አጠር ያለ ገለጻ በማድረግ ተሳታፊዎች በቂ መነሻ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ከዚህ በመቀጠል ስልጠናው በአካል ጉዳተኞች መብት ጥበቃና አካቶ ረገድ ሰፊ ልምድና አውቀተ ባላቸው ፕሮፌሰር በላይ አሰልጣኝነት ሙሉ ቀን ተካሂዷል። የሥልጠናው ተሳታፊዎች የባንክ ሥራ አስኪያጆችና የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞች ሲሆኑ 14 ከሚሆኑ ባንኮች በጠቅቅላላ 23 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ፤ ሲቢኢ (3)፣ ዳሸን ባንክ (2)፣ አዋሽ ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ አሮሚያ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ቡና ባንክ እና ከአማራ ባንክ (2) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
መልካም ጅምሮች
– ብዙ ባንኮች ከአገልግሎት ልህቀት/ Excellence አንጻር አካታች ፖሊስ ሲኖራችው በተለይ ንግድ ባንክ ልምዱን ያካፈለ ሲግሆን ለቀጣይ አካታችነት መደላደል ይሆናል
– በባንኮች ሰራተኞች በኩል ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ችግር መኖሩ ተነስቷል
– የባንክ አካታችነት እና ተደራሽነት ለአይነ-ስውራን በከተማ ደረጃ መሻሻሎች የሚታይ ሲሆን ነገር ግን በድጂታል አገልግሎት መሰራትና ተከታታይ ግንዛቤ የፈልጋል
– ከማህበራዊ ተቋማትና አካል – ጉዳተኛ ድርጅቶች ጋር ያለው ግንኙነት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ባንኮች ያላችው አካታችነት ግንዛቤ ላይ ተጽኖ መኖሩን ተመልክቷል
– የባንኮች ህንጻ ተደራሽነት ችግር ያለበት ሲሆን ነገር ግን በባንኮች አካታች ፖሊሲ አንዱ መሟላት የሚገባው ነገር መሆኑን የባንክ ማኔጅመንት ክትትል ይፈልጋል፤ ከባላ ድረሻ አካላት የወትወታ ስራ በቀጣይ መሰራት አለበት
ማጠቃለያ ፡
ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ተሳታፊዎች በሀላፊነት ያላችውን የባንክ ስራዎች በመታግስ ለሙሉ ቀን እስክ 11 ስአት ድረስ በንቃት በመሳተፍ በስልጠናው ደስተኛ፡ ጠቃሚና እና በቀጣይ አስፈላጊውን ትብብር የአገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት እንዲሁም በጋራ ለመስራት እንደሚተጉ ቃል በመግባት ተጠናቋል።


Leave a Reply